ለወራት ጠፈር ላይ እንዲቆዩ የተገደዱት ጠፈርተኞች ለገና በዓል መልካም ምኞት ላኩ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) መንኮራኩራቸው በገጠማት የቴክኒክ ችግር ምክንያት ጠፈር ላይ ለወራት እንዲቆዩ የተገደዱት የአሜሪካ የጠፈር ምርምር ጣቢያ (ናሳ) ጠፈርተኞች ለገና በዓል መልካም ምኞታቸውን ለወዳጅ ዘመዶቻቸው ልከዋል፡፡
ሱኒታ ዊልያምስ፣ ባሪ ዊልሞር፣ ዶን ፔቲት እና ኒክ ሄግ የተባሉት እነዚህ ጠፈርተኞች በፈረንጆቹ አቆጣጠር ሰኔ 5 ቀን2024 ለስምንት ቀናት የሙከራ በረራ ለማድረግ ወደ ጠፈር ጉዞ ያደረጉ ቢሆንም በመንኮራኩራቸው ላይ በተፈጠረ የቴክኒክ ችግር ምክንያት ለወራት በዛው የጠፈር ጣቢያ እንዲቆዩ ግድ ሆኗል፡፡
ጠፈርተኞቹ በመካከላቸው የቴክኒክ እገዛ የሚያደርጉላቸው በርካታ ሰዎች እንዳሉና በመልካም ሁኔታ ላይ መሆናቸውን ከጣቢያው ወደ ምድር በላኩት ተንቀሳቃሽ ምስል መልዕክት ገልጸዋል፡፡
በዓሉን እንደማንኛውም ከቤተሰብ ርቆ እንደሚኖር ሰው በጥሩ ሁኔታ እያከበርን ነው ሲሉም መግለጻቸውን ስካይ ኒውስ ዘግቧል፡፡