Fana: At a Speed of Life!

ብሪክስ 9 ሀገራትን በአጋርነት እንደሚቀበል ተነገረ

 

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 15፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በፈረንጆቹ 2025 መባቻ ብሪክስ ዘጠኝ ሀገራትን በአጋርነት እንደሚቀበል ተገለፀ፡፡

በሶስት አህጉራት የሚገኙት አዲስ አጋር ሀገራቱ ቤላሩስ፣ ቦልቪያ፣ ኢንዶኖዥያ፣ ካዛኪስታን፣ ኩባ፣ ማሌዥያ፣ ታይላንድ፣ ኡጋንዳ እና ኡዝቤከስታን መሆናቸው ታውቋል፡፡

የአዲስ አጋር ሀገራቱ የአባልነት ጥያቄ ቀደም ሲል በሩሲያ ካዛን በተካሄደው 16ኛው የብሪክስ የመሪዎች ጉባኤ ላይ መፅደቁ ነው የተገለፀው፡፡

የብሪክስ አጋር ለመሆን ከ30 በላይ ሀገራት ጥያቄ አቅርበው እንደነበር የተገለፀ ሲሆን አዲሶቹ ዘጠኝ ሀገራት በብሪክስ መሪዎች ተገምገመው የአጋርነት ጥያቄአቸው ተቀባይነት ማግኘቱ ተመላክቷል፡፡

በቅርቡም ተጨማሪ አራት ሀገራት ብሪክስን በአጋርነት ይቀላቀላሉ ተብሏል፡፡

በብራዚል፣ ሩሲያ፣ ህንድ፣ ቻይና እና ደቡብ አፍሪካ የተመሰረተው የብሪክስ የኢኮኖሚ ቡድን በፈረንጆቹ 2024 ኢትዮጵያን ጨምሮ አራት ሀገራትን በአባልነት መቀበሉ ይታወሳል።

አዳዲስ አባል ሀገራት መቀላቀላቸውን ተከትሎም 9 አባላት የነበሩት ብሪክስ የኢኮኖሚ ቡድን ዘጠኝ አጋሮችን ለመቀበል መዘጋጀቱን ኢራን ፕሬስ እና አር ቲ ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.