የሶማሊያ ልዑክ ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ይገባል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሶማሊያ የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ኦማር የተመራ የሶማሊያ ሪፐብሊክ ልዑክ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት ዛሬ ምሽት አዲስ አበባ ይገባል።
የልዑኩ የአዲስ አበባ ጉብኝት በዋናነት በቅርቡ በኢትዮጵያና በሶማሊያ መንግስት መካከል የተደረሰውን የአንካራ ስምምነት ለማጠናከር ያለመ መሆኑ ተመላክቷል፡፡
ልዑኩ በአዲስ አበባ በሚኖረው ቆይታ የኢትዮጵያና የሶማሊያ ግንኙነትን ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ ምክክር እንደሚያደርግ ተጠቁሟል፡፡
በተጨማሪም ልዑኩ ከኢትዮጵያ አቻው ጋር በሁለቱ ሀገራት ትብብር፣ የእርስ በርስ መከባበር እንዲሁም በቀጣናዊ እና ዓለም አቀፋዊ የጋራ ፍላጎቶ ላይ ውይይት ያደርጋል መባሉን ከሶማሊያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡