Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድን አቀናጅቶ በመገንባት ላይ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል የከተሞችን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ መሰረተ ልማቶችን አቀናጅቶ በመገንባት የህዝብ ፍላጎት ለማሟላት እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ማማሩ አያሌው (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ከ400 ሚሊየን ብር በላይ በጀት እየተከናወኑ ያሉ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ እና የንፁህ መጠጥ ውሃ ፕሮክቶች ተጎብኝተዋል።

በደብረብርሃን ከተማ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ የሚሰራው ዘመናዊ የፍሳሽ ቆሻሻ ማስወገጃ ፕሮጀክቱ 50 በመቶ ግንባታው መጠናቀቁ በጉብኝቱ ወቅት ተገልጿል፡፡

በዚሁ ወቅት ማማሩ አያሌው(ዶ/ር)÷ በክልሉ የከተሞችን የንጹህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት እና የፍሳሽ ቆሻሻ አወጋገድ የህዝብ ጥያቄ አጣጥሞ ለመመለስ እየተሰራ መሆኑ አስረድተዋል፡፡

በደሴ፣ በጎንደርና በደብረብርሃን ከተማ በዓለም ባንክ የገንዘብ ድጋፍ ዘመናዊ የፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጀክቶች እየተተገበሩ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡

በደብረብርሃን እየተገነባ የሚገኘውን የፍሳሽ ማስወገጃ ፕሮጀክት በጥራት እየተሰራ እንደሚገኝ መመልከታቸውን አንስተዋል፡፡

በተመሳሳይ ከ90 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ ግንባታው የተጠናቀቀውን የንጹህ የመጠጥ ውሃ ፕሮጀክት መጎብኘታቸውን ጠቁመዋል፡፡

የደብረብርሃን ከተማ ተቀዳሚ ከንቲባ በድሉ ውብሸት በበኩላቸው÷ በፍሳሽ ማስወገጃ ችግር የከተማው ህዝብ በተደጋጋሚ ቅሬታ ያነሳ እንደነበር አስታውሰዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.