Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 14፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሔራዊ ተሃድሶ ኮሚሽን ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ተወካዮች ጋር የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ማቋቋም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ውይይት አካሂዷል፡፡

በውይይታቸውም በቀጣይ በክልሉ ያሉ የቀድሞ ተዋጊዎችን መልሶ ለማቋቋምና ወደ ማህበረሰቡ ለመቀላቀል በጋራ መስራትና በስኬት መፈጸም በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

በውይይት መድረኩ አጠቃላይ የኮሚሽኑ እቅድ፣ የፕሮግራሙ ይዘት፣ የአተገባበር ስልትና የባለድርሻ አካላት ሚና ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

በተጨማሪም የመስክ ምልከታ የተካሄደ ሲሆን÷በቀጣይ ፕሮግራሙ በክልሉ በሚገኙ የተመረጡ ማዕከላት ውስጥ እንደሚጀመር መጠቀሱን የኮሚሽኑ መረጃ ያመላክታል፡፡

ለመርሐ ግብሩ ስኬት የክልሉ ሕዝብና መንግስት እንዲሁም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪ ቀርቧል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.