Fana: At a Speed of Life!

በኦሮሚያ ክልል የተለያዩ ዞኖች ህዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ደቡብ ምዕራብ ሸዋ፣ምስራቅ ወለጋ፣ምስራቅ ሸዋ፣ምዕራብ ጉጂ፣ምስራቅ ቦረና ፣ቄለም ወለጋ እና በአርሲ ዞኖች ህዝባዊ ሰልፎች ተካሄዱ።
የሰልፉ ተሳታፊዎች ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የተጀመረው ጥረት ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
ተሳታፊዎቹ የሰላም መንገድ ሁሌም አሸናፊ ነው፣የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበላችሁ እናመሰግናን የቀራችሁትም ይህን መንገድ ተከተሉ የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶችን አስተላልፈዋል፡፡
ለሀገር ሰላም ያለብንን ሃላፊነት እንወጣለን ፣ክልላችን ሰላም ይሻል እንዲሁም ሰላማችን እንዲረጋገጥ በጋራ እንሰራለን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡
በሰልፎቹ ላይ አባገዳዎች፣ ሀደ ስንቄዎች፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶችን ጨምሮ የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተሳትፈዋል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.