Fana: At a Speed of Life!

ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በምክክሩ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን- ሰኚ ነጋሳ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 13፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲሳተፉ ጥሪ እናቀርባለን ሲሉ የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ሰኚ ነጋሳ ገለፁ።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት አባላት በምክክሩ እየተሳተፉ ሲሆን÷የዜጎችን ሰላም ለማስፈን በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለው ምክክር አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት ከፍተኛ አመራር ሰኚ ነጋሳ÷የምክክሩን አስፈ
ላጊነት አፅንኦት ሰጥተው፣ የኦሮሞ ህዝብም ምክክሩ ሰላም ያመጣል የሚል እምነት እንዳለው ገልፀዋል፡፡
ምክክሩ ምሉዕ የሚሆነው ሁሉም ዜጋ ሲሳተፍበት መሆኑን የተናገሩት አመራሩ÷ለዚህም ታጥቀው የሚንቀሳቀሱ ሁሉ እንደነሱ የሰላም ስምምነት ፈፅመው በምክክር መድረኩ እንዲሳተፉ ነው ጥሪ ያቀረቡት፡፡
በምክክር መድረኩ ሃሳቦችን በነፃነት አንስተን፣ ሰላማዊ በሆነ መንገድ ተከራክረን፣ ለዜጎች ሰላምና ደህንነት የሚጠቅሙ ሀሳቦችን ይዘን ስንወጣ ነው ምክክሩ የተሳካ የሚሆነው ያሉት ሰኚ ነጋሳ÷ ለዚህም ሁላችንም ለምክክሩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ብለዋል፡፡
የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን መድረኩን በማመቻቸቱ ምስጋና ማቅረባቸውንም ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ ያመለክታል፡፡
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.