የፌዴሬሽኑ 28ኛው ጠቅላላ ጉባዔ መካሄድ ጀመረ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 12፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን 28ኛው ጠቅላላ ጉባዔ መካሄድ ጀምሯል።
ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ÷አትሌቲክስ ኢትዮጵያን በዓለም አደባባይ በማስተዋወቅ ትልቅ ሚና ያለውና ከውድድር በላይ መሆኑን ገልጸዋል።
መንግስት ለዘርፉ ልዩ ትኩረት እንደሚሰጠውም ነው የተናገሩት፡፡
በጉባዔው የ27ኛ መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ቃለ ጉባዔ የፀደቀ ሲሆን÷ የፌዴሬሽኑ ያለፉት አራት ዓመታት የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት እየቀረበ ይገኛል።
በወርቅነህ ጋሻሁን