Fana: At a Speed of Life!

እየታየ ያለው የበጋው ደረቅና ፀያማ የአየር ሁኔታ ቀጣይነት ይኖረዋል

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 11፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሚቀጥሉት አሥራ አንድ ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የበጋው ደረቅና ፀያማ የአየር ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው የኢትዮጵያ ሜቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ገለጸ።

 

በተጠቀሱት ቀናት በአብዛኛው የሀገሪቱ አካባቢዎች ላይ የበጋው ደረቅ፤ ጸሀያማውና ነፋሻማው የአየር ሁኔታ ይኖራቸዋል፡፡

 

ይሁን እንጂ በፀሀይ ኃይል ታግዘው ከሚፈጠሩት የሚቲዎሮሎጂ ገጽታዎች ላይ በመነሳት በደቡብና ደቡብ ምዕራብ የአገሪቱ አካባቢዎች ላይ የደመና ሽፋን ይኖራቸዋል ነው የተባለው፡፡

 

ከዚሁ ጋር ተያይዞ በተለይም በደቡብ ምዕራብና በጋ ሁለተኛ የዝናብ ወቅታቸው በሆኑት የሀገሪቱ አካባቢዎች ማለትም የሶማሌ ክልል ደቡባዊ ክፍል፣ የጉጂና የቦረና ዞኖች፣ የሲዳማ ክልል፣ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ዞኖች አልፎ አልፎ በሚኖሩት ቀናት አነስተኛ መጠን ያለው ዝናብ እንሚያገኙ ተገልጿል፡፡

 

ሌላ በኩል በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው የሀገሪቱ ክፍሎች ላይ እየታየ ያለው የበጋው ደረቅና ፀያማ የአየር ሁኔታ ቀጣይነት እንደሚኖረው የሚጠበቅ ሲሆን÷ በአንዳንድ ደጋማ አካባቢዎች ላይ ግን የሌሊቱ እና የማለዳው ቅዝቃዜ በአንፃሩ እንደሚቀንስ ከኢንስተትዩቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.