Fana: At a Speed of Life!

በክልሉ ከዋናው መስመር ውጪ 1 ነጥብ 3 ሚሊየን አባዎራዎችን የተለያዩ የሃይል አማራጮች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 10፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በኦሮሚያ ክልል ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው የሚገኙ ዜጎችን የተለያዩ የሃይል አማራጮችና የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የክልሉ ውሃና ኢነርጂ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በቢሮው የኢነርጂ ሃብት ልማት ዳይሬክተር አቶ ተስፋዬ ሶሬሣ እንዳሉት÷በኦሮሚያ ክልል የኤሌክትሪክ ሃይል አቅርቦት ተደራሽነትን ለማስፋት በትኩረት እየተሰራ ነው፡፡

አሁን ላይ አጠቃላይ በክልሉ ያለው የኤሌክትሪክ ሃይል ተደራሽነት 49 ነጥብ 8 በመቶ መድረሱን ነው የገለጹት፡፡

ቢሮው በተለይም ከዋናው የኤሌክትሪክ መስመር ርቀው የሚገኙ የማህበረሰብ ክፍሎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት እየሰራ መሆኑን አንስተዋል፡፡

በዚህም 1 ነጥብ 3 ሚሊየን አባዎራዎችን የተለያዩ የሃይል አማራጮችና የኢነርጂ ቴክኖሎጂዎች ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን አመልክተዋል፡፡

ከሶላር፣ ከባዮ ጋዝ እና ከተለያዩ ምንጮች የሚገኘውን ሃይል ለማሳደግም ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በትብብር እንደሚሰራ አብራርተዋል፡፡

ከዋናው መስመር ርቀው የሚገኙ ዜጎችን የኤሌክትሪክ ተጠቃሚነት ይበልጥ ለማስፋትም አጋር አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቀዋል።

በመላኩ ገድፍ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.