Fana: At a Speed of Life!

በፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ውስጥ ተጉዘው መዳብ ሰርቀዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቆሻሻ ፍሳሽ ማስወገጃ ቱቦ ጉድጓድ ውስጥ ለውስጥ ሁለት ኪሎ ሜትር ተጉዘው 500 ኪሎ ግራም መዳብ ሰርቀዋል የተባሉ አምስት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተገለጸ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ ወንጀሉን የፈፀሙት በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ 6 ጉምሩክ ጀርባ በሚገኘው የኢትዮጵያ ባሕር ትራንዚት ግቢ ውስጥ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በዚህም አፋ (ኦቼ) የምግብ ማቀነባበሪያ ፋብሪካ አካባቢ በሚገኘው የፍሳሽ ማስወገጃ ጉድጓድ ገብተው ውስጥ ለውስጥ በመጓዝ የጉምሩክ ኮሚሽን አስቀምጧቸው ከነበሩ ኮንቴይነሮች አንደኛውን ከፍተው 500 ኪሎ ግራም መዳብ ሰርቀው በፍሳሽ ማስወገጃው ጉድጓድ ሲወጡ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.