Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የዳያስፖራ ተሳትፎ ዘርፍ ልምዷን ለታንዛኒያ አካፈለች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ በዳያስፖራ ማሕበረሰብ ልማት እና ተሳትፎ ሥራ ያላትን ልምድ ለታንዛኒያ አካፈለች።

19 አባላት ያሉት የታንዛኒያ የፓርላማ አባላት፣ የመንግሥት ሥራ ኃላፊዎች እና በኢትዮጵያ የታንዛኒያ ኤምባሲ ልዑክ በኢትዮጵያ ዳያስፖራ አገልግሎት የልምድ ልውውጥ አድርጓል፡፡

የዳያስፖራ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ፍጹም አረጋ የሁለቱን ሀገራት ጠንካራ ወዳጅነት አውስተው÷ የኢትዮጵያን የዘርፉን ተሞክሮ ለመካፈል መምጣታቸውን አድንቀዋል፡፡

የልዑኩ መሪ ፍሎረንት ላውረንት ክዮምቦ በበኩላቸው÷ ኢትዮጵያ ለአፍሪካ ነጻነት በተደረገ ትግል ብቻ ሳይሆን በልዩ ልዩ ዘርፎች ተቋማዊ አሠራርን በማስፈን ረገድ ፋና ወጊ መሆኗን አንስተዋል፡፡

የዳያስፖራ ተሳትፎን ከማሳደግ አንጻርም በኢትዮጵያ እየተከናወኑ ካሉ ውጤታማ ሥራዎች ልምድ ለመቅሰምና ቀጣይነት ያለው ትስስር ለመፍጠር ወደ ኢትዮጵያ መምጣታቸውን አስረድተዋል፡፡

የልምድ ልውውጡ የታንዛኒያ መንግሥት የዳያስፖራ ተሳትፎን ለማትጋት የጀመራቸውን ጥረቶች ለማሳደግ የሚያግዙ ተሞክሮዎችን ለመቅሰም እንደሚያስችልም ገልጸዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.