Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በተለያዩ ከተሞች የተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ ተጠናቀቀ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአማራ ክልል በተለየዩ ከተሞች የተካሄደው ሕዝባዊ ሰልፍ በስኬት መጠናቀቁን የክልሉ ፖሊስ አስታውቋል፡፡

የክልሉ ፖሊስ ባወጣው መግለጫ÷ የአማራ ክልል ሕዝብ ለዓመታት የተደቀነበትን የሰቆቃ ቀንበር የሚያወግዝ ሰላማዊ ሰልፍ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ ሃሳብ በተለያዩ ከተሞች ማካሄዱን አንስቷል፡፡

ለዓመታት ክልሉ በራሱ አለሁ ባይ ጽንፈኛ ሃይሎች ምክንያት በሰቆቃ ሕይወት ውስጥ እንዲጓዝ፣ እንዲዘረፍ፣ እንዲፈናቀልና እንዲሰደድ መደረጉን ጠቁሟል፡፡

ይህን የመከራ ቀንበር የተሸከመው የክልሉ ሕዝብ የሰላም ካውንስል እስከመወከል የደረሰ “ሰላሜን መልሱልኝ” ጥያቄውን ከጀመረ መሰነባበቱን ጠቅሷል፡፡

ይሁን እንጂ ጽንፈኛው ሃይል የማህበረሰብን የሰላም ጥያቄ “ጆሮ ዳባ ልበስ…” በማለት ከሰብል ማቃጠል ጅምሮ የክልሉን ህዝብ ባህልና ወግ የማይገልጽ፣ ዘመኑን የማይመጥንና ፀያፍ ተግባር መፈጸሙንም አስታውሷል፡፡

በዛሬው ዕለትም የጽንፈኛውን ተግባራት የሚያወግዝ ሰልፍ በተለያዩ የክልሉ ከተሞች ተካሂዶ በስኬት መጠናቀቁን ፖሊስ አስታውቋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.