Fana: At a Speed of Life!

የሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ለመቻልና ለተመጣጠነ ምግብ አቅርቦት ወሳኝ ሚና ይጫወታል – የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 9፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የሌማት ትሩፋት በምግብ ራስን ለመቻልና የተመጣጠነ ምግብ አቅርቦትን በቤትና በሀገር ደረጃ ለማረጋገጥ ወሳኝ ሚና እንደሚጫወት የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት አስታውቋል፡፡

ጽ/ቤቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በ2015 ዓ.ም ሀገር በቀሉን የሌማት ትሩፋት መርሐ ግብር ማስጀመራቸውን አስታውሷል፡፡

መርሐ ግብሩ በአራት አመታት የሥራ እቅድ የወተት እና ወተት ተዋፅዖ፣ ዶሮ፣ የእንቁላል፣ የማርና የአሳ ምርቶችን ምርት ብሎም ምርታማነት ማሳደግ ላይ ያተኮረ እንደነበር ጠቅሷል፡፡

መርሐ ግብሩ በትልቅ ደረጃ ከሚመረቱት ባሻገር በአነስተኛ የመኖሪያ ቤት ደረጃ የሚደረጉ እንደ የጓሮ ዶሮ ርባታ፣ አነስተኛ የአሳ ምርት ሥራና የንብ ማነብ እንቅስቃሴዎችን የመደገፍ ሥራ እንደሚሰራም አስገንዝቧል፡፡

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.