ቪኒሺየስ ጁኒየር የፊፋ የአመቱ ምርጥ ተጫዋች ሆኖ ተመረጠ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ)ብራዚላዊው የሪያል ማድረዱ ተጫዋች ቪኒሽየስ ጁኒየር የ2024 የፊፋ የወንዶች ምርጥ ተጫዋች ተብሎ ተመረጠ።
ተጫዋቹ በውድድር ዓመቱ ለሪያል ማድሪድ የስፔን ላሊጋንና የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ዋንጫ እንዲያሸንፍ ከፍተኛ አስተፅኦ አድርጓል።
ተጫዋቹ ለቡድኑ 24 ጎሎችን አስቆጥሮ 11 ለግብ የሚሆኑ ኳሶች አመቻችቶ አቀብሏል።
በ2024 በወንዶች የፊፋ ምርጥ 11 ተጫዋች ዝርዝር ውስጥ የአሰቶን ቪላው በረኛ ኤሚ ማርቲኔዝ ሲመረጥ፣ በተከላካይ ስፍራ የአርሰናሉ ዊሊያም ሳሊባ፣ የማንችስተር ሲቲው ሩበን ዲያዝ፣ እንዲሁም የሪያል ማድሪዶቹ ሩዲገርና ዳኒ ካርቫሃል ተመርጠዋል።
ከአማካኝ ስፍራ ተጫዋቾች ደግሞ ቶኒ ክሩዝ፣ ሮድሪ እና ጁድ ቤሊንግሃም ሲመረጡ በአጥቂ ስፍራ ቪኒሽዬስ ጁኒዬር፣ ኧርሊንግ ሃላንድ እና የባርሴሎናው ታዳጊ ላሚን ያማል ሆነው መመረጣቸውን ፊፋ አስታውቋል።
በሴቶች ደግሞ ስፔናዊቷ አይታና ቦንማቲ ሽልማቱን አሸንፋለች።
ጣሊያናዊው የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ካርሎ አንቸሎቲም የፊፋ የአመቱ ምርጥ አሰልጣኝ በመሆን ተመርጠዋል፡፡
በተመሳሳይ የማንቼስተር ዩናይትዱ የክንፍ ተጫዋች አሌሀንድሮ ጋርናቾ ኤቨርተን ላይ ያስቆጠራት ግብ የፊፋ የዓመት ምርጥ ግብ ሽልማት አሸንፏል።