Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 8፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ እና ታንዛኒያ በተለያዩ ዘርፎች በጋራ ለመሥራት የሚያስችላቸውን ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

ስምምነቱ የተደረገው በኢትዮ ታንዛኒያ የጋራ የሚኒስትሮች ኮሚሽን ውይይት ላይ ሲሆን÷ በዚሁ ወቅት ሀገራቱ በቀጣይ በተለያዩ ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆናቸውን አረጋግጠዋል፡፡

በስምምነቱ በሰላም እና ፀጥታ፣ ኢኮኖሚ ፣ቱሪዝም፣ ግብርና፣ ኢንቨስትመንትና መሰል ዘርፎች ላይ በጋራ ለመሥራት የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)÷ የሀገራቱ በቅንጅት መሥራት አልሸባብን ጨምሮ ሌሎች ሽብርተኞችን ለመከላከል ብሎም ሰላም በአኅጉሪቱ እንዲሰፍን አስቻይ ሁኔታዎችን ይፈጥራል ብለዋል።

የታንዛኒያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እና የምሥራቅ አፍሪካ የትብብር ሚኒስትር አምባሳደር መሐሙድ ተሀቢት ኮምቦ በበኩላቸው ÷ በሀገራቱ መካከል ያለውን የሕዝብ ለሕዝብ ግንኙነት ለማጠናከር የቪዛ ክልከላን ማንሳት ይገባል ብለዋል፡፡

በፍቅርተ ከበደ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.