Fana: At a Speed of Life!

ሻንዶን ግዛት ለኦሮሚያ ክልል በትምህርት ዘርፍ ድጋፍ እንደምታደርግ ገለጸች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ሽመልስ አብዲሳ በሻንዶን ግዛት ምክትል አስተዳዳሪ ጁጂ ሶን ከተመራ ልዑክ ጋር ተወያይተዋል፡፡

በውይይታቸውም በአሮሚያ ክልል እና ሻንዶን ግዛት መካከል በሚኖረው ትብብር እና የልማት እድሎች ዙሪያ መክረዋል፡፡

በውጪ ቀጥታ ኢንቨስትመንት፣ በኢንዳስትሪ ፓርክ ልማት እንዲሁም በኢኮኖሚና የንግድ ትስስር ላይ በጋራ ለመስራት በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይም ተወያይተዋል፡፡

አቶ ሽመልስ ክልሉ በዚህ ረገድ የሚገኙ እድሎችን ለማልማት የሚያስችል ሁኔታ ለመፍጠር ዝግጁ መሆኑን አረጋግጠዋል፡፡

ኦሮሚያ ክልል በትምህርት እና በሙያ ስልጠና በትብብር የመስራ ፍላጎት እንዳለው ጠቁመው÷የሻንዶን ግዛት  ልዑካን ለክልሉ መምህራን የትምህርት እድል ለመስጠት ቃል መግባታቸውን ጠቁመዋል፡፡

በቀጣይም በኦሮሚያ ክልል እና በቻይናዋ ሻንዶን ግዛት አስተዳደር መካከል የእህትማማችነት ፊርማ ለመፈራረም ስምምነት ላይ መደረሱን ርዕሰ መስተዳድሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.