Fana: At a Speed of Life!

በአማራ ክልል በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ የተሳታፊ እና የአጀንዳ ልየታ ይደረጋል-ኮሚሽኑ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 7፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተሳታፊ እና የአጀንዳ ልየታ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ ይህን ያለው የኦሮሚያ ክልል ሀገራዊ ምክክር የአጀንዳ የማሰባሰብ ምዕራፍ በአዳማ ከተማ በተጀመረበት መድረክ ላይ ነው።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር መሥፍን አርኣያ(ፕ/ር) በዚህ ወቅት ÷ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የዘገየው የአጀንዳ ማሰባሰብ እና የተሳታፊዎች ልየታ በቀጣይ አንድ ወር ጊዜ ውስጥ እንደሚደረግ አስታውቀዋል፡፡

ኮሚሽኑ በእስካሁን ቆይታው በዘጠኝ ክልሎች እና ሁለት ከተማ አሥተዳደሮች የአጀንዳ ልየታ ሥራ ማከናወኑንም መግለጻቸውን አሚኮ ዘግቧል።

በ971 የኢትዮጵያ ወረዳዎች የተሳታፊዎች ልየታ መከናወኑንም ዋና ኮሚሽነሩ አስታውሰዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.