Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫን በመከተል ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው – ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር)

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ኢትዮጵያ የብዝሃ ዘርፍ የኢኮኖሚ አቅጣጫን በመከተል ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች ነው ሲሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) ገለጹ፡፡

ለገሰ ቱሉ (ዶ/ር) በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ክልል ሚዛን አማን ከተማ የተለያዩ ልማት ስራዎችን እየጎበኙ ነው፡፡

በጉብኝታቸውም የሚዛን ቡና ቅምሻና ሰርትፊኬሽን ማዕከል፣ የሚዛን አማን ዱቄት ፋብሪካንና በግል ባለሀብት በግንባታ ላይ የሚገኘውን የሙፍቲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።

ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት ÷ኢትዮጵያ በብዝሃ ዘርፍ ኢኮኖሚ አቅጣጫ በመመራቷ ፈጣን የኢኮኖሚ እድገት እያስመዘገበች እንደምትገኝ ገልጸዋል፡፡

ለየኢኮኖሚ ዘርፎቹ የተስተካከለ አቅጣጫና ስትራቴጂ በማስቀመጥ እና በብቃት መተግበር መቻሏ ውጤታማ እንዳደረጋትም ጠቁመዋል፡፡

ስኬቷም በአለማቀፍ ተቋማት ሳይቀር የተረጋገጠ መሆኑን ያነሱት ሚኒስትር÷አለም አቀፉ የገንዘብ ተቋም እና አለም ባንክ በፈረንጆቹ አቆጣጠር በ2024 በጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት ኢትዮጵያን ከአምስቱ የአፍሪካ ምርጦች ውስጥ አንዷ እንደሆነች ይፋ ማድረጋቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡

በግብርናው ዘርፍ በመኸር አዝመራ፣ በበጋ መስኖ እና በበልግ አዝመራ ስንዴን ጨምሮ ለአምስት ዋና ዋና ሰብሎች የተለየ ትኩረት በመሰጠቱ ምርታማነት እንዲጨምር ማድረጉንም አስገንዝበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.