የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ለሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገቡ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአልጄሪያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አሕመድ አታፍ ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አዲስ አበባ ገብተዋል።
ሚኒስትሩ ቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴዔታ አምባሳደር ብርቱካን አያኖ እና ሌሎች የሚኒስቴሩ ከፍተኛ አመራሮች አቀባበል አድርገውላቸዋል።
አሕመድ አታፍ በአዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታ ከመንግሥት ከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር በሁለትዮሽና ዓለም አቀፋዊ ጉዳዮች ዙሪያ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።