የኡጋንዳ መከላከያ ሠራዊት ምክትል አዛዥ የኢትዮጵያ አየር ኃይልን ጎበኙ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኡጋንዳ መከላከያ ሠራዊት ምክትል አዛዥ ሌተናል ጄኔራል ሳም ኦኪዲንግ እና ልዑካቸው የኢፌዴሪ አየር ኃይልን ወታደራዊ አቅሞች ጎብኝተዋል፡፡
በጉብኝታቸውም የአየር ኃይልን ከባድ ጥገና ማዕከል፣ የአየር ኃይልን አካዳሚ የበረራ ትምህርት ቤት እና መሰል ወታደራዊ አቅሞችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
ጉብኝቱ የሁለቱ ሀገራት ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች በተለያዩ ወታደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመስራት መስማማታቸውን ተከትሎ መደረጉን የመከላከያ ሰራዊት መረጃ ያመላክታል፡፡