የቴክኒክ ችግር ያጋጠመው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን በሰላም ማረፉ ተገለጸ
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 6፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የበረራ ቁጥሩ ET 612 የሆነ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ተመልሶ በሰላም ማረፉን አየር መንገዱ አስታወቀ።
ትናንት ታህሳስ 05 ቀን 2017 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ወደ ዱባይ በሚያደርገው በረራ ከተነሳ ከ30 ደቂቃ በኋላ የቴክኒክ ችግር ስላጋጠመው ወደ አዲስ አበባ ተመልሶ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ በሰላም አርፏል።
ለጥንቃቄ ሲባል መንገዶች እና የበረራ ሠራተኞች በአስቸኳይ ከአውሮፕላኑ እንዲወርዱ መደረጉም ተገልጿል።
ዘወትር ለመንገደኞቹ ደህንነት ቅድሚያ እንደሚሰጥ የገለጸው አየር መንገዱ፤ መንገደኞች ለደረሰባቸው መጉላላት አየር ይቅርታ ጠይቋል።
የቴክኒክ ችግሩ በመጣራት ላይ እንደሆነም አመልክቷል።