Fana: At a Speed of Life!

የታንቡራ ካምፕ ዓድዋ ካምፕ በሚል ተሰየመ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 5፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በተባበሩት መንግሥታት የደቡብ ሱዳን ሰላም ማስከበር ተልዕኮ የ19ኛ ሞተራይዝድ ሻለቃ የግዳጅ ቀጣና የሆነውን የታንቡራ ካምፕ ዓድዋ ካምፕ በሚል ስያሜ እንዲጠራ ወሰነ።

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ኃይል በደቡብ ሱዳን ለታምቡራ ሰላምና መረጋጋት እያበረከተ ለሚገኘው አስተዋጽኦ ካምፑ ዓድዋ በሚል ስያሜ እንዲጠራ መወሰኑን የመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ መረጃ አመላክቷል፡፡

የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ግዳጁን በላቀ ብቃት የሚወጣና ስኬታማ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን፥ በተሰማራበት አስቸጋሪ የግዳጅ ቀጣና ዳግማዊ ዓድዋ ድል በማስመዝብ ላይ እንደሚገኝም ተጠቁሟል፡፡

ዓድዋ የኢትዮጵያውያን የአንድነትና የፅናት ተምሳሌት መሆኑም ነው የተመላከተው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.