Fana: At a Speed of Life!

የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ እና የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 4፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያ እና የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ (ካዛብላንካ ስቶክ ኤክስቼንጅ) ስትራቴጂካዊ የትብብር ስምምነት ተፈራረሙ፡፡

በስምምነቱ መሰረት የካዛብላንካ አክሲዮን ገበያ የኢትዮጵያ ሠነደ ሙዓለ-ንዋዮች ገበያን የቴክኒክ እና የሥራ አቅም የሚያሳድጉ ድጋፎችን ያደርጋል።

ተቋሙ ደኅንነቱን የጠበቀ እና ቀልጣፋ የንግድ ሥርዓት እንዲፈጥር የቴክኖሎጂ ማዕቀፉን፣ የአሠራር አቅም እና የአደጋ አሥተዳደር አቅሙን የሚያጎለብቱ ሥራዎች እንደሚያከናውን ተገልጿል።

ስምምነቱ ሁለቱ ተቋማት ምርቶችን በጋራ ማልማትን ጨምሮ በተለያዩ መስኮች የጋራ ፕሮጀክቶችን ቀርጸው እንዲሠሩ ያስችላቸዋል መባሉን በራባት የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ አመላክቷል፡፡

ተቋማቱ በዓለም አቀፍ እና ቀጣዊ መድረኮች አፍሪካ ያሏትን ፍላጎቶች ለማንጸባረቅ እንደሚሠሩም ነው የተገለጸው፡፡

የአፍሪካ ገበያ ትስስር እና ልማት ለማሳለጥ የሚያስችሉ የመፍትሔ ሐሳቦችን በጋራ እንደሚያፈልቁም ተነግሯል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.