በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የነበረ 5 ሺህ 500 ሊትር ቤንዚን ተያዘ
አዲስ አበባ፣ ታኅሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ አቃቂ ቃሊቲ ክ/ከተማ ከ2 ጄ አር ማደያ በሕገ-ወጥ መንገድ ተቀድቶ ሲዘዋወር የነበረ 5 ሺህ 500 ሊትር ቤንዚን መያዙን የከተማ አስተዳደሩ ንግድ ቢሮ አስታውቋል፡፡
በሕገ-ወጥ መንገድ ሲንቀሳቀስ የተያዘው ቤንዚን በሕጉ መሰረት እንደሚወረስና ማደያውም እንደሚታሸግ ተገልጿል፡፡
በማደያው ላይ የሚወሰደው እርምጃ ሌሎች መሰል ሕገ-ወጥ ተግባር እንዳይፈፅሙ ማስተማሪያ እንደሚሆንም መጠቆሙንም የቢሮው መረጃ አመልክቷል፡፡