Fana: At a Speed of Life!

የብሪክስ ሀገራት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ በጋራ ሊሰሩ ነው

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 3፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የብሪክስ አባል ሀገራት በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዘርፍ በጋራ በመስራት በቴክኖሎጂ ትብብር ዙሪያ ያላቸውን አጋርነት ሊያጠናክሩ መሆኑ ተሰምቷል፡፡

የሩሲያ ቀጥተኛ ኢንቨስትመንት ፈንድ በብሪክስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ የጋራ ልማት ላይ ያተኮረ ጥምረት ይፋ አድርጓል፡፡

የሩሲያ ቀጥታ ኢንቨስትመንት ፈንድ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ኪሪል ዲሚትሪቭ፣ ከሩሲያ፣ ቻይና፣ ሕንድ፣ ብራዚል፣ ኢራን እና የተባበሩት አረብ ኢሚሬቶች የተውጣጡ ከ20 በላይ ኩባንያዎች የብሪክስ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስን ህብረትን ተቀላቅለዋል፡፡

ከእነዚህ ኩባንያዎች መካከል ዩኒቨርሲቲዎች፣ የህክምና ኩባንያዎች፣ የፋርማሲዩቲካል አልሚዎች፣ የፋይናንሺያል መሠረተ ልማት አልሚዎች፣ የቴሌኮሙኒኬሽን ፈጠራ ባለሙያዎች፣ የኤሌክትሪክ ባትሪዎች አምራቾች እና ሴሚኮንዳክተሮች እንደሚገኙበትም ነው የተናገሩት፡፡

ጥምረቱ የብሪክስ አባል ሀገራት የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቡድን ቴክኖሎጂዎችን በበለጠ ፍጥነትና አቅም የጋራ ልማትን እንዲያዳብሩ ያስችላል መባሉን የዘገበው አር ቲ ነው፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.