Fana: At a Speed of Life!

በተደረገ ክትትል አደንዛዥ ዕጽን ጨምሮ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በአዲስ አበባ ኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ቢራ ሰፈር አካባቢ ፖሊስ ባደረገው ጥናትና ክትትል አደንዛዥ ዕጽን ጨምሮ በርካታ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ፡፡

ከጉዳዩ ጋር በተያያዘም አምሥት ተጠርጣሪዎች መያዛቸውን የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

በግለሰቦቹ መኖሪያ ቤት በተደረገ ፍተሻም በኮንትሮባንድ የገባ 7 ሺህ 730 ፍሬ ሞባይል፣ በሁለት ፌስታል የተጠቀለለ ካናቢስ፣ ፍላት ቴሌቪዥን፣ ላፕቶፕ፣ በርካታ የአሜሪካ ዶላር፣ በርካታ ማዳበሪያ ቶርሽን ጫማ እና አንድ ማዳበሪያ አልባሳት ተገኝቷል ተብሏል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.