Fana: At a Speed of Life!

ቱርክሜኒስታን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን አስታወቀች

አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) ቱርክሜኒስታን ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ግንኙነት ለማጠናከር እና ኤምባሲዋንም ለመክፈት ቁርጠኛ መሆኗን የሀገሪቱ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

በፓኪስታን የኢትዮጵያ አምባሳደር ጀማል በከር (ዶ/ር) ከቱርክሜኒስታን ምክትል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርዳር ሙሃመዱርዲዬቭ ጋር በሁለትዮሽ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተዋል፡፡

በዚሁ ወቅት ኢትዮጵያ ከጎረቤት ሀገራት ጋር በትብብር መንፈስና ወንድማማችነት በሚያጠናክር መልኩ እየሠራች መሆኗን አምባሳደሩ አስረድተዋል፡፡

ለቀጣናው ሰላምና መረጋጋት ሽብርተኝነትን በመዋጋት ረገድም ከፍተኛ መስዋትነት እየከፈለች እንደምትገኝ ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ በበኩላቸው ሀገራቱን በተለያዩ ዘርፎች በማቀራረብ በአጋርነት ለመሥራት እንዲያስችል በአዲስ አበባ ኤምባሲ ለመክፈት ዝግጅት እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል፡፡

አስቀድመውም ከፍተኛ የመንግሥት ባለስልጣናትን ያካተተ ልዑክ በኢትዮጵያ ለሥራ ጉብኝት እንደሚልኩ ጠቁመዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.