በሻምፒየንስ ሊጉ ጁቬንቱስ ከማንቼስተር ሲቲ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል
አዲስ አበባ፣ ታሕሣሥ 2፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ስድስተኛ ዙር ሁለተኛ ቀን ጨዋታዎች ሲቀጥሉ ጁቬንቱስ ከማንቼስተር ሲቲ እንዲሁም ቦሩሺያ ዶርቱመንድ ከባርሴሎና የሚያደርጉት ፍልሚያ ይጠበቃል፡፡
ምሽት 2 ሠዓት ከ45 ላይ አትሌቲኮ ማድሪድ ከስሎቫን ብራቲስላቫ እንዲሁም ሊል ከሰትሩም ግራዝ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በሌላ የጨዋታ መርሐ-ግብር ምሽት 5 ሠዓት ቱሪን አሊያንዝ ስታዲየም ላይ ጁቬንቱስ ከማንቼስትር ሲቲ እንዲሁም ሲግናል ኢዱና ፓርክ ላይ ቦሩሺያ ዶርቱመንድ ከባርሴሎና የሚያደርጉት ግጥሚያ የምሽቱ ተጠባቂ ጨዋታ ነው፡፡
በተመሳሳይ ምሽት 5 ሠዓት ላይ ኤሲሚላን ከሬድስታር ቤልግሬድ፣ አርሰናል ከሞናኮ፣ ቤኔፊካ ከቦሎኛ፣ ፌይኑርድ ከስፓርታ ፕራግ እንዲሁም ስቱትጋርት ከያንግ ቦይስ ይጫወታሉ፡፡
ትናንት ምሽት ተጠባቂ በነበሩ የአውሮፓ ሻምፒየንስ ሊግ የምድብ ጨዋታዎች ማሸነፍን ብቸኛ አማራጩ አድርጎ ወደ ሜዳ የገባው ሪያል ማድሪድ አተላንታን 3 ለ 2 ረትቷል፡፡
የማድሪድን ግቦችም ኪሊያን ምባፔ፣ ቪኒሺየስ ጁኒየር እና ጁድ ቤሊንግሃም ሲያስቆጥሩ÷ የአተላንታን ግቦች ደግሞ ዲ ካትሌየር እና ሉክማን ከመረብ አሳርፈዋል፡፡
እንዲሁም ሊቨርፑል ዢሮናን 1 ለ 0፣ ባየርሊቨርኩስን ኢንተርሚላንን 1 ለ 0፣ ብረስት ፒኤስቪን 1 ለ 0፣ ክለብ ብሩጅ ስፖርቲንግ ሊዝበንን 2 ለ 1፣ አስቶንቪላ አርቢ ሌብዢግን 3 ለ 2፣ ፒኤስጂ ሬድ ቡል ሳልዝበርግን 3 ለ 0፣ ባየርንሙኒክ ሻክታር ዶኔስክን 5 ለ 1 ሲያሸንፉ÷ ዳይናሞ ዛግሬብ እና ሴልቲክ ያለ ምንም ግብ አቻ ተለያይተዋል፡፡