Fana: At a Speed of Life!

በሱዳን በደረሰ የቦምብ ጥቃት የ28 ሰዎች ህይዎት አለፈ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 30፣ 2017 (ኤፍ ኤም ሲ) በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም በነዳጅ ማደያ ላይ በደረሰ የቦምብ ጥቃት 28 ሰዎች ሲሞቱ 37 ሰዎች ቆስለዋል፡፡

የደቡብ ካርቱም የድንገተኛ አደጋ ክፍል በሰጠው መግለጫ በነዳጅ ማደያው ላይ በተወረወረ ቦምብ ነው አደጋው የደረሰው፡፡

ይህም የ28 ሰዎችን ህይዎት በመቅጠፍ ከ37 በላይ በሚሆኑ ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል ጉዳት ከማድረሱ ባለፈ ከፍተኛ የንብረት ውድመት ማስከተሉ ተነግሯል፡፡

ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ህክምና እየተደረገ ቢሆንም ተጨማሪ የህክምና እርዳታ ድጋፍ ተጠይቋል ያለው የዥንዋ ዘገባ፤ ለደረሰው ጥቃት ሃላፊነት የወሰደ አካል እንደሌለ አመልክቷል።

ሱዳን ከፈረንጆቹ 2023 ሚያዝያ አጋማሽ ጀምሮ በሁለት ሃይሎች መካከል በተቀሰቀሰ ግጭት ላይ እንደምትገኝ ይታወቃል፡፡

በግጭቱ ከ27 ሺህ 120 በላይ ሰዎች ለህልፈት ሲዳረጉ፥ ከ14 ሚሊየን በላይ ሰዎች ደግሞ ከአካባቢያቸው ለመፈናቀል ተገደዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.