Fana: At a Speed of Life!

በሐረሪ ክልል 38 ሺህ ተማሪዎች የምገባ ተጠቃሚ መሆናቸው ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በሐረሪ ክልል የተጀመረው የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብር 38 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ ማድረጉን የክልሉ ርዕሰ መሥተዳድር ኦርዲን በድሪ አስታወቁ፡፡

ርዕሰ መሥተዳድሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሑፍ÷ ከሰው ተኮር የማኅበራዊ ብልጽግና ሥራዎቻችን ውስጥ አንዱ የሰው ኃብት ልማት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

በዚህ ረገድ በክልሉ የተጀመረው የትምህርት ቤት ምገባ መርሐ-ግብር 38 ሺህ ተማሪዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አንስተዋል፡፡

መርሐ-ግብሩ የትምህርት ተሳትፎን በመጨመር፣ መጠነ-መቅረትና ማቋረጥን ከመቀነሱም በላይ የተማሪዎችን የትምህርት ቅበላ እንደሚጨምር የጥናቶች ውጤቶች ማመላከታቸውን ጠቁመዋል፡፡

ይህ መርሐ-ግብር አቅመ ደካማ የማኅበረሰብ ክፍሎችን ከትምህርት ገበታ እንዳይርቁ እገዛ የሚያደርግ ስለሆነ÷ ከባለድርሻ አካላት ጋር በመቀናጀት ዘላቂነቱን ማረጋገጥና ማስፋት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

 

 

 

 

 

 

 

 

 

All reactions:

9494

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.