Fana: At a Speed of Life!

ሩሲያና ዩክሬንን ለማሸማገል የሚያስችል መነሻ ሀሳብ ተቀረጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ሩሲያ እና ዩክሬንን ለማደራደር ተመራጩ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ያዋቀሩት ቡድን ሁለቱን ወገኖች ለማሸማገል የሚያስችል መነሻ ሀሳብ መቅረጹ ተነገረ።

በሶስት የዶናልድ ትራምፕ አዳራዳሪ የቡድን አባላቶች በተዘጋጀው መነሻ ሀሳብ ሀገራቱን ለማሸማገል በሚደረገው ጥረት የሰሜን አትላንቲክ ጦር ቃል ኪዳን (ኔቶ) አባል ሀገራት እንደማይሳተፉበት ተመላክቷል፡፡

የመጀመሪያው የማሸማገያ መነሻ ሀሳብ ትራምፕ የሩሲያ እና ዩክሬን ቋሚ መልዕክተኛ አድርገው በሾሟቸው ኬት ኬሎግ ቀርቧል።

መነሻ ሀሳቡ ሩሲያ ከተቆጣጠረቻቸው የዩክሬን ግዛቶች ሳትልቅ ተኩስ አቁም እንዲደረግ የሚያስችል ምክረ ሀሳብ እንደተካተተበት ተናግረዋል።

ዩክሬን የኔቶ አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ ውድቅ እንደሚሆንም ጠቅሰዋል፡፡

ምክረ ሀሳቡ በምስራቃዊ ዩክሬን በሁለቱም ሀገራት የማይተዳደሩ ራስ ገዝ ክልሎችን ለመፍጠር ያለመ ስለመሆኑም ተጠቁሟል።

በሶስተኛነት የቀረበው ምክረ ሀሳብ ደግሞ የድርድር እቅድ ሲሆን በዚህም በሀገራቱ ድንበር አካባቢዎች ወታደራዊ እንቅስቃሴ እንዳይኖር የሚያደርግ መሆኑ ተገልጿል።

የሩሲያ የውጭ መረጃ አገልግሎት ሀላፊ ሰርጌይ ናሪሽኪን÷ የትራምፕ አደራዳሪ ቡድን ያቀረበው መነሻ ሀሳብ ሩሲያ በዩክሬን ላይ ወታደራዊ ብልጫ እንዳላት የሚያሳይ ነው ብለዋል፡፡

ድርድሩ ምንም ይሁን ምን ሩሲያ በዩክሬኑ ጦርነት ጥቅሟን ታስከብራለች ማለታቸውን ሬውተርስ እና ጂኦፖለቲክስ ዘግበዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.