Fana: At a Speed of Life!

በጃል ሰኚ ነጋሳ የተመሩ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት ከከንቲባ አዳነች አቤቤ ጋር ተወያዩ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ከኦሮሚያ ክልል መንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ላይ የደረሰው በኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት ከፍተኛ አመራር ጃል ሰኚ ነጋሳ የተመራ የሠራዊቱ አባላት በአዲስ አበባ የዓድዋ ድል መታሰቢያን እና ሌሎች የልማት ሥራዎችን ጎብኝተዋል፡፡

ከውይይቱ በኋላም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ እንኳን ወደ ሰላም መንገድ መጣችሁ በማለት ተቀብለው አነጋግረዋቸዋል፡፡

የሰላም መንገድ አማራጭ የሌለው እና ሁሉንም ተጠቃሚ የሚያደርግ መንገድ መሆኑን በመረዳት መንግስት ላደረገው ጥሪ የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት አባላት የሰጡት ምላሽ የሚያስመሰግን መሆኑን ከንቲባዋ አንስተዋል፡፡

ስምምነቱ የፖለቲካ እና የሃሳብ ልዩነቶችን ዘመናዊ በሆነ መንገድ በውይይትና በሰላም መፍታት ለሌሎችም አርአያ የሚሆን ተግባር መሆኑን ገልጸዋል::

ጃል ሰኚ ነጋሳ በበኩላቸው÷ለተደረገላቸው አቀባበል አመስግነው የሰላም ጥሪውን የተቀበሉት የህዝብን ጉዳት ለመቀነስ እና የሰላም አማራጭን መቀበል ብልህነትና አዋቂነት መሆኑን በመረዳታቸው እንደሆነ መናገራቸውን የከንቲባ ጽ/ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.