የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ወደ ተዘጋጀላቸው ማዕከላት መግባታቸውን ቀጥለዋል
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 25፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በተለያዩ አካባቢዎች ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጁላቸው ማዕከላት መግባታቸውን ቀጥለዋል፡፡
የኦሮሚያ ክልል መንግሥት እና የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አመራሮች ባሳለፍነው እሁድ የደረሱትን የሰላም ስምምነት ተከትሎ ትናንት ሠራዊቱ ወደ ማዕከላት መግባት መጀመራቸው ይታወቃል፡፡
በዛሬው ዕለትም በተለያዩ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት አባላት ወደ ተዘጋጁላቸው ማዕከላት መግባት መቀጠላቸውን በብልጽግና ፓርቲ የኦሮሚያ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡
የሠራዊቱ አባላት ወደ ማዕከላቱ በሚያደርጉት ጉዞም ሕዝቡ አቀባበል እያደርገላቸው መሆኑ ተገልጿል፡፡