Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮጵያና እና ቻይና በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 24፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያና እና ቻይና በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር እየተሰራ መሆኑን የጉምሩክ ኮሚሽን ገልጿል፡፡

የቻይና ጉምሩክ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያዎች በተለያዩ ዘርፎች ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና በዛሬዉ እለት መሰጠት ጀመሯል፡፡

በስልጠናው መክፈቻ ስነ-ስርዓት ላይ የኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የህግ ተገዥነት ዘርፍ ምክትል ኮሚሽነር አቶ አዝዘው ጫኔ ÷ በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ተወካዮች፣ የሻንጋይ ጉምሩክ ዩኒቨርሲቲ ምሁራን እንዲሁም ሰልጣኞች ተገኝተዋል፡፡

አቶ አዝዘው ጫኔ በዚህ ወቅት ÷የጉምሩክ ተቋማት ኢኮኖሚያዊ እድገትን ለማምጣት፣ የንግድ መሳለጥን እውን ለማድረግ እንዲሁም በሀገራት መካከል ያለውን ድንበር ዘለል ግንኙነት ለማጠናከር ያላቸው ፋይዳ ከፍተኛ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስልጠናው ኢትዮጵያና ቻይና በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጎልበት እንዲሁም በዘርፉ ያሉ እውቀቶችን ለመቅሰም እና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚያስችልም መግለጻቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ጸኃፊ ጂያንግ ዡ በበኩላቸው ÷የቻይና መንግስት የአፍሪካ የጉምሩክ ተቋማትን ዐቅም ለመገንባት የሚያስችል ፕሮግራም በመቅረጽ እየሰራ መሆኑን ገልጸው ለኢትዮጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን ከፍተኛ ባለሙያዎች የሚሰጠው የዐቅም ግንባታ ስልጠናም የዚሁ አንድ አካል መሆኑን ተናግረዋል ፡፡

ከስልጠና ባሻገር ኢትዮጵያና እና ቻይና በጉምሩክ ዘርፍ ያላቸውን ትብብር ለማጠናከር የሚያስችሉ በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ መሆኑንም አንስተዋል፡፡

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.