ኢትዮጵያ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከዩኔስኮ ተረከበች
አዲስ አበባ፣ 23 ሕዳር፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮጵያ የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራ ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ተረክባለች።
በሕንድ ኒው ዴልሂ በተካሄደው 46ኛው የዩኔስኮ የዓለም ቅርስ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ነው ኢትዮጵያ በባህል ቅርስነት ያስመዘገበችውን የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ሥፍራን ሕጋዊ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ከድርጅቱ የዓለም ቅርስ ማዕከል ዳይሬክተር ላዛሬ ኤሎውዶ አሶሞ የተቀበለችው፡፡
ኢትዮጵያ ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የመልካ ቁንጡሬ ባልጪት የአርኪዮሎጂ እና ፓሊዮንቶሎጂ ስፍራን በባህል ቅርስነት ማስመዝገቧን በፓሪስ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ መረጃ ያመላክታል፡፡