Fana: At a Speed of Life!

በማህበራዊ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና በኢትዮጵያ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (ዩኤስኤይድ) በማህበራዊ ዘርፎች ላይ በትብብር ለመሥራት የሚያስችል ውይይት አካሄዱ።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር) እና በኢትዮጵያ የዩኤስኤይድ ዳይሬክተር ስኮት ሆክላንደር በወጣቶች ስብዕና ማጎልበቻ፣ ወላጆቻቸውን ያጡ ህፃናትን በበጎ ፈቃድ አገልግሎት መደገፍ፣ ወጣቶች ላይ ትኩረት ባደረገው “ዩ ሪፖርት” ላይ በትብብር መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ መክረዋል፡፡

እንዲሁም የሥራ ሃላፊዎቹ በሴቶች ግብርና ተጠቃሚነት፣ በሴቶች ዲጂታል ግብርና፣ በማህበራዊ ጥበቃ ኮንፈረንስ እና በሌሎች ጉዳዮች ላይ አብሮ ለመሥራት የሚያስችል ውይይት አድርገዋል።

በውይይቱ ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ተግባራዊ እያደረገች ባለው ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ሪፎርም ላይ ድርጅቱ እያደረገ የሚያደርገውን ድጋፍ አድንቀዋል።

በተለይም የሴቶችን ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተዘጋጁ ፕሮጀክቶች እንዲደገፉ መጠየቃቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡

ስኮት ሆክላንደር በበኩላቸው÷በማህበራዊና ተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ በጋራ ለመሥራት ፍላጎት እንዳለ ገልጸዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.