የኢትዮጵያ አየር መንገድ ባልደረባ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ ዶላር ለባለቤቱ አስረከቡ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 23፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ የሴኪዩሪቲ ክፍል ባልደረባ ፍሬዘር በቀለ ወድቆ ያገኙትን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ለባለቤቱ አስረከቡ፡፡
ገንዘቡን አቶ ፍሬዘር ሕዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ከመንገደኛ ወድቆ ማግኘታቸውን አየር መንገዱ አስታውቋል፡፡
ግለሰቡ በኢትዮጵያዊ ጨዋነትና ሲቀጠሩ በገቡት ቃል መሰረት አየር መንገዱ የሚመራበትን መርህና ሥነ-ምግባር እንዲሁም ሙያዊ ታማኝነታቸውን በብቃት መወጣታቸውንም አስታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እና ሥነ-ምግባር የተላበሰ የደንበኞች አገልግሎት ለመስጠት ሁሌም እንደሚተጋ ነው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ ያስታወቀው፡፡