Fana: At a Speed of Life!

የአየር ኃይሉ 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነገ ይከበራል

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 19፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር ኃይል 89ኛ ዓመት የምስረታ በዓል “የተከበረች ሀገር የማይበገር አየር ኃይል” በሚል መሪ ሀሳብ ነገ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል።

የበዓሉ አካል የሆነ የዋዜማ ዝግጅት ቢሾፍቱ በሚገኘው የአየር ኃይል ጠቅላይ መምሪያ እየተካሄደ ነው።

በዝግጅቱ የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሀኑ ጁላ፣ የአየር ኃይሉ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳን ጨምሮ የመከላከያ ከፍተኛ ጦር መኮንኖች፣ የአፍሪካ ሀገራት አየር ኃይል አዛዦች የሌሎች የፀጥታ ተቋማት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

በዋዜማ ዝግጅቱ አየር ኃይልን ወደ ከፍታ ለመውሰድ በሚደረጉ ጥረቶች የተለያዩ ተሳትፎ ያደረጉ እና የደገፉ ግለሰቦች፣ ድርጅቶችና ተቋማትም ዕውቅና ተሰጥቷል፡፡

የኢትዮጵያ አየር ኃይል ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል ይልማ መርዳሳ በዚህ ወቅት ÷አየር ሃይሉ ከለውጡ በኋላ በዘመናዊ መልኩ መገንባቱን ገልጸዋል።

በለውጡ ዓመታት በጥናት ላይ በመመርኮዝ ቴክኖሎጂ በሚሸከም የሰው ኃይል፤ በዘመናዊ ትጥቅ፣ በውጊያ መሰረተ ልማት እንዲሁም አየር ኃይሉ ለሁሉም መስክ ምሳሌ የሆነ ተቋም በሚያደርጉ ሥራዎች ላይ በትኩረት መሰራቱንም አንስተዋል ።

የአየር ሃይሉን ነባር አውሮፕላኖችና ቴክኖሎጂዎች በማሻሻል እንዲሁም አዲስ በማምረት በሁሉም ረገድ ዘመኑ የደረሰበት የሀገር አለኝታ የሆነ ጠንካራ ተቋም መገንባት ችለናል ብለዋል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.