የኢትዮጵያ እና ርዋንዳን ግንኙነት ለማጠናከር ያለመ ውይይት ተደረገ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስትር ብናልፍ አንዱዓለም ከርዋንዳ የውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር ቪንሰንት ቢሩታ (ዶ/ር) ጋር የሁለትዮሽ ትብብርን ለማጠናከር ያለመ ውይይት አደረጉ፡፡
በውይይታቸውም የሀገራቱን ጥቅም ባስጠበቀ መልኩ የጋራ ልምድንና ዕውቀትን በመጠቀም ለሰላም ግንባታ ሥራዎች ውጤታማ ተግባር ለማከናወን የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መምከራቸውን የሰላም ሚኒስቴር መረጃ አመላክቷል፡፡