ምክር ቤቱ የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት አጸደቀ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 6ኛ መደበኛ ስብሰባ የቀረበለትን የ2017 በጀት ዓመት የፌዴራል መንግሥት ተጨማሪ 582 ቢሊየን ብር በጀት አጽድቋል፡፡
የተጨማሪ በጀት ረቂቁን በምክር ቤቱ የመንግስት ዋና ተጠሪ ሚኒስትር ተስፋዬ ቤልጂጌ (ዶ/ር) አቅርበዋል።
የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሺዴም በጉዳዩ ላይ ከምክር ቤት አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ምክር ቤቱም በተጨማሪ በጀቱ ላይ ከተወያየ በኋላ በሦስት ተቃውሞ እና በአምስት ድምጸ-ተአቅቦ በአብላጫ ድምጽ በጀቱን አጽድቆታል።
በለይኩን ዓለም