ከ403 ሚሊየን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ተያዙ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 17፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ጉምሩክ ኮሚሽን ከሕዳር 6 እስከ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ባደረገው ክትትል 403 ነጥብ 4 ሚሊየን ብር ግምታዊ ዋጋ ያላቸው የኮንትሮባንድ ዕቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ተያዙ፡፡
በተጨማሪም የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 26 ተጠርጣሪ ግለሰቦች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው እና 20 ተሽከርካሪዎች መያዛቸውን የኮሚሽኑ መረጃ አመላክቷል፡፡
ከተያዙት የኮንትሮባንድ ዕቃዎች መካከልም÷ አልባሳት፣ ኤሌክትሮኒክስ፣ የግንባታ ዕቃዎች፣ ቡና፣ ጥራጥሬ፣ የተሽከርካሪ መለዋወጫ፣ የመዋቢያ ዕቃዎች፣ ጫት፣ አደንዛዥ እጾች፣ መድኃኒት፣ የምግብ ዘይት፣ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች፣ የውጭ ሀገር ገንዘቦች እና የጦር መሳሪያዎች እንደሚገኙበት ተገልጿል፡፡
በተጠቀሰው የጊዜ ገደብ የገቢ እና የወጭ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር÷ አዲስ አበባ ኤርፖርት፣ ኮምቦልቻ እና ድሬዳዋ ጉምሩክ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች ቀዳሚውን ስፍራ መያዛቸው ተጠቅሷል፡፡