Fana: At a Speed of Life!

በባሌ ዞን 22 ሺህ የንብ ቀፎ ለአርሶአደሩ መድረሱ ተገለፀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 15፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን 22 ሺህ የንብ ቀፎ ለአርሶአደሩ መድረሱ ተገለፀ፡፡

በመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት አስተባባሪነት ከተለያዩ የመገናኛ ብዙሃን የተውጣጡ ባለሙያዎች በባሌ ዞን ጎባ ወረዳ የሌማት ቱሩፋት ስራዎችን ጎብኝተዋል።

በዞኑ ወጣቶችን በማደራጀትና አርሶ አደሮችን በተናጠል የማር ምርት ላይ እንዲሰማሩ መደረጉንና በዞኑ በተያዘው ዓመት ብቻ 22 ሺህ የንብ ቀፎ ለአርሶ አደሩ መዳረሱ ተገልጿል፡፡

በዚህም 6 ሺህ ቶን የማር ምርት እንደሚጠበቅ የዞኑ አስተዳዳሪ አብድልሃኪም አሊይ ተናግረዋል፡፡

በዞኑ ማርን ከማምረት ባለፈ በማጥራት ስራ ላይ የተሰማሩ አርሶ አደሮች ወደ ውጭ መላክ መጀመራቸውም ተመላክቷል፡፡

አርሶ አደሮቹ በበኩላቸው ÷በማር ምርት ስራ ላይ በመሰማራታቸው በህይወታቸው ለውጥ ማምጣታቸው ገልጸው ከማር ምርት በተጨማሪ የጓሮ አትክልት በማምረት ተጠቃሚ መሆናቸውንም ተናግረዋል

በፈቲያ አብደላ

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.