የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል እየተከበረ ነው
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 14፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የብልጽግና ፓርቲ 5ኛ ዓመት የምስረታ በዓል በዓድዋ ድል መታሰቢያ እየተከበረ ነው።
በዓሉ “የሃሳብ ልዕልና ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሃሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
በአከባበር ሥነ-ሥርዓቱ የብልጽግና ፓርቲ ም/ፕሬዚዳንትና በም/ጠቅላይ ሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ሃላፊ አደም ፋራህ፣ የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት አፈ ጉባዔ ታገሰ ጫፎ እና የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባዔ አገኘሁ ተሻገር ተገኝተዋል፡፡
በተጨማሪም የፌዴራል ተቋማት የብልጽግና ፓርቲ አስተባባሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ ዓለሙ ስሜን (ዶ/ር) ጨምሮ የብልጽግና ፓርቲ ከፍተኛ አመራሮችና ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።