Fana: At a Speed of Life!

የሶማሌ ክልል የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ጸደቀ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የሶማሌ ክልል ሥራ አስፈፃሚ ምክር ቤት የክልሉን የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ አጸደቀ።

ምክር ቤቱ ባካሄደው 4ኛ መደበኛ ጉባኤ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ያቀረበው የትምህርትና ስልጠና ፖሊሲ ላይ ተወያይቶ ምክረ ሃሳቦችን በማከል ፖሊሲው እንዲጸድቅ ውሳኔ አሳልፏል።

ፖሊሲው በክልሉ ትምህርት በተለይም ከ1ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ትምህርት ሂደትን ለማሻሻል ያለመ መሆኑ ተገልጿል።

ዕውቀትና መልካም ሥነ-ምግባር የተላበሰ ትውልድ ለመፍጠር ፖሊሲው ከፍተኛ አስተዋጽኦ ያደርጋል መባሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.