Fana: At a Speed of Life!

ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ሃይል ባለፉት ሦስት ወራት ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር ገቢ ማግኘቱን አስታወቀ፡፡

የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዕቅድ አፈፃፀም ገምግሟል።

በአፈጻጸም ሪፖርቱ እንደተገለጸው፤ ለመደበኛና ለካፒታል ፕሮጀክቶች ማስፈፀሚያ 110 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር ፀድቆ ወደ ሥራ ተገብቷል።

ባለፉት ሦስት ወራት ተቋሙ ከሀገር ውስጥ የኃይል ሽያጭ 8 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር እንዲሁም ለውጭ ሀገር እና ለዳታ ማይኒንግ ከቀረበ ኃይል 59 ነጥብ 42 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ገቢ ማግኘቱ በሪፖርቱ ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ በሩብ ዓመቱ ከኃይል ሽያጭ ያገኘው ገቢ ከዕቅዱ አንፃር የ13 በመቶ ብልጫ ያለው ሲሆን ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር የ36 በመቶ ጭማሪ አሳይቷል ተብሏል።

በበጀት ዓመቱ ከ7 ሺህ 200 ሜጋ ዋት በላይ የማመንጨት አቅም ያላቸው የአምስት ኃይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ግንባታ እየተከናወነ መሆኑንም የተቋሙ መረጃ አመላክቷል።

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.