Fana: At a Speed of Life!

በአርሲ ዞን 930 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑ ተገለጸ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 13፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን 930 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን የዞኑ ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

የተለያዩ መገናኛ ብዙሃን ጋዜጠኞች በአርሲ ዞን ሌሞ ቢልቢሎ ወረዳ እየለሙ የሚገኙ የተለያዩ ሰብሎችን ጎብኝተዋል፡፡

የአርሲ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ሃላፊ ገና መሃመድ በዚህ ወቅት÷በዞኑ በመኸር እርሻ 930 ሺህ ሄክታር መሬት በሰብል መሸፈኑን ገልፀዋል፡፡

ከአጠቃላይ የሰብል ሽፋኑ ውስጥ 451 ሺህ ሄክታር መሬት በስንዴ የተሸፈነ ሲሆን÷ከስንዴ ምርት 16 ሚሊየን ኩንታል ምርት ይገኛል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

177 ሺህ ሄክታር ደግሞ በቢራ ገብስ ምርት መሸፈኑን ጠቁመው÷ከዚህም 6 ነጥብ 9 ሚሊየን ኩንታል ይገኛል ተበሎ እንደሚጠበቅ አንስተዋል፡፡

የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴዔታ ከበደ ዴሲሳ ÷ በገብስ ምርት ልማት ላይ በተደረገ ርብርብ ከውጭ ይገባ የነበረውን የቢራ ገብስ ሙሉ በሙሉ በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን ተናግረዋል።

በፈቲያ አብደላ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.