የጎንደር ከተማ አሥተዳደር በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሱ አውቶብሶችን ተረከበ
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) የጎንደር ከተማ አሥተዳደር በኤሌክትሪክ ኃይል የሚንቀሳቀሱ የከተማ አውቶብሶችን ተረክቧል።
የከተማ አውቶብሶቹ በበላይነህ ክንዴ ቢዝነስ ግሩፕ የተገጣጠሙ ሲሆን ፥126 ሚሊየን ብር ወጪ እንደተደረገባቸው እንዲሁም ነዳጅ እና ዘይት የማይጠቀሙ እንደሆኑም ተገልጿል፡፡
ከተማዋን ለማዘመን በሚደረገው ጥረት ውስጥ የዘመኑ ቴክኖሎጂን መጠቀም የቱሪስት ተመራጭነቷን የሚያሳድግ ነውም ተብሏል።
ባለሃብት በላይነህ ክንዴ በተገኙበት በዛሬው እለት የኤሌትሪክ አውቶብሶችን ርክክብ ተደርጓል።
ባለሃብቱ በላይነህ ክንዴ በርክክቡ ወቅት ÷ አውቶብሶቹ ለከተማዋ ቱሪዝም እድገትና ለነዋሪዎችም የተስማሙ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
ድርጅታቸው ከጎንደር ከተማ ልማት ጋር አብሮ እንደሚሰራና የልማት ክፍተቶችን እንደሚሞላም አንስተዋል፡፡
በበረከት ተካልኝ