የ59 ዓመቷ ካናዳዊት በ1 ስዓት ከ1ሺህ 500 በላይ ፑሻፖች በመስራት ክብረ-ወሰን ሰበረች
አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) ዶናጄን ዊልዴ የተባለችው የ59 ዓመቷ ካናዳዊት በ1 ስዓት ከ1ሺህ 500 በላይ ፑሻፖች በመስራት የዓለም ክብረ ወሰን መስበሯ ተሰምቷል፡፡
ይህች ሴት በአንድ ስዓት ውስጥ 1ሺህ 575 ፑሻፖች የሰራች በዓለም የመጀመሪያዋ ሴት በመሆን በጊነስ ሪከርድስ ስሟን አስመዝግባለች፡፡
ዶናጄን ዊልዴ ከዚህ በፊት የነበረውን ሪከርድ በ17 ደቂቃ ቀድማ በማሻሻል የዓለም ክብረ-ወሰን የሰበረች በእድሜ ትልቋ ሴት መሆኗን ዩፒአይ ዘግቧል፡፡
ዊልዴ ለጂኔስ ወርልድ በሰጠችው ቃለ-መጠይቅ በስዓቱ በጣም ጠንካራና ጥሩ አቅም ስለነበረኝ በቀጣዮቹ 17 ደቂቃዎች ከዚህ የተሻለ ቁጥር ያለው ፑሻፕ እሰራለሁ ብዬ አስቤ ነበር ብላለች፡፡
ዊልዴ ከዚህ ቀደም “በአብዶሚናል ፕላንክ ፖዚሽን” ውድድር 4 ስዓት ከ30 ደቂቃ ከ11 ሰከንድ በመቆየት ረጅሙን ስዓት በማስመዝገብ ብቸኛዋ ሴት ባለ ክብረ-ወሰን ነበረች ብሏል ዘገባው፡፡
ለዚህ ውድድር ያደረገቸው ልምምድ ለዚህኛው ሪከርድ ምክንያት እንደሆነላትም ተናግራለች፡፡