Fana: At a Speed of Life!

11ኛው ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማሕበረሰብ አገልግሎት ስልጠና ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ሕዳር 12፣ 2017 (ኤፍ ቢ ሲ) 11ኛው ዙር የብሔራዊ በጎ ፈቃድ ማሕበረሰብ አገልግሎት ስልጠና ተጀምሯል፡፡

የሠላም ሚኒስቴር ከወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር ነው ሥልጠናውን የሚሰጠው።

የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጉቼ ጉሌ (ዶ/ር)÷ ኢትዮጵያውያን እንደ ሀገር አንዱ ለሌላው የመድረስ፣ የደከመውን የመደገፍ ባሕል ያለን ሕዝቦች ነን ብለዋል።

ለዘመናት የተሻገረ ማንነታችንን አዘምነን በብሔራዊ ደረጃ ወጥ በሆነ መንገድ እንደ በጎ እሴት አበልፅገን ለማስቀጠል በሠላም ሚኒስቴር አስተባባሪነት የሚሰጥ ስልጠና በተገቢው ማስኬድ አስፈላጊ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

የሠላም ሚኒስትር ደኤታ ከይረዲን ተዘራ (ዶ/ር) በበኩላቸው÷ በአስር ዙሮች ከ75 ሺህ በላይ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማሰልጠን ወደ ማሕበረሰቡ እንዲቀላቀሉና እንዲያገለግሉ መደረጉን ገልፀዋል።

የበጎ ፈቃደኝነት አገልግሎት አስፈላጊነት ከፍ ማለቱን ጠቅሰው፤ በ11ኛው ዙር 1 ሺህ 500 ወጣቶች ከተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በመመልመል በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ ስልጠና እንዲካፈሉ ተደርጓል ነው ያሉት።

በመለሰ ታደለ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.